#የአማራ_ተጋድሎ ከየት ወዴት?

amhara
ethiopia
የአማራ_ተጋድሎ

(Admin) #1

1983 ዓ.ም. ለእኛ ለአማሮች :- ወገኖቻችን በጅምላ የሚታረዱበትን፣ በገፍ የሚፈናቀሉበትንና በዘረኞች ያለማቋረጥ የሚሰቃዩበትን ዘመን ያዋለደ ክፉ ዘመን ነው፡፡ ይህ ጊዜ የአማራ ሕዝብ ከጨለማ ወደ ባሳ ጨለማ የገባበት፣ በሕዝባችን ላይ የታወጀው የጥፋት ደወል የተደወለበት፣ በርካቶች በአማራነታቸው የታረዱበት፣ ቤት ንብረታቸውን በትነው ለዘመናት ከኖሩባቸው አካባቢዎች የተፈናቀሉበትና በአገራቸው ባይተዋር ሆነው እንዲኖሩ የተወሰነበት የክፉ ጊዜ መጀመሪያ ነው፡፡ በደርግ አምባገነናዊ አገዛዝ ልጆቹን ሲነጠቅ የኖረው፣ ከየትኛውም ሕዝብ በላይ ልጆቹን ለጦርነት እንዲያዋጣ ሲገደድ እና በኮታ፣ በግብር ወ.ዘ.ተ. ሲማቅቅ የቆየው ሕዝባችን፣ ከመከራ ወደ ባሰ መከራ እንዲገባ የተደረገበት ጊዜም ነው፡፡

ነብሰ ገዳዩ የወያኔ ቡድን ንጹሗን አማሮችን እያደነ እንደጨፈጨፈ፣ ከቤት ንብረታቸው እንዳፈናቀለ፣ ሁለም ሕዝብ በአማራ ላይ እንዲዘምት ሰነድ አዘጋጅቶና የመንግሥት በጀት በጅቶ እንደቀሰቀሰ፣ ተስፋ የሚጣልባቸውን የአማራ ልጆች እስር ቤት እያጎረ የቶርቸር ሰለባ ሲያደርግ እንደቆየ ወዘተ አይዘነጋም፡፡ በሚያሳዝን መልኩ፣ የአማራ ሕዝብ በዚህ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ መጠነ ሰፊ ውርጅብኝ ሲወርድበት የቆየ እና አሁንም ይኸው የዘር ማጥፋት ጦርነት ግልጽ በሆነ መልኩ ታውጆ የቀጠለ ቢሆንም፣ ለሕዝባችን የሚጮህለት ኃይል የለም፡፡ የሕዝባችን በደል የሚገደው ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ድርጅትም አልተገኘም፡፡ የዚህ ነብሰ ገዳይ ቡድን ወዳጅ የሆኑ ኃያላን አገሮችም በሕዝባችን ላይ የታወጀውን የዘር ፍጅት እያዩ እንዳላዩ ማለፍን መርጠዋል፡፡ በአጭሩ ለአማራ ሕዝብ ከራሱ ውጪ ማንም እንደማይጮህለት፣ ማንም እንደማይገደው በሚገባ ተረጋግጧል፡፡ ለአማራ ሕዝብ የምንታገልበት ምክንያት ይህ ነው – ራሳችንን ከጥፋት ለማዳን፡፡

Download the full article in PDF #የአማራ_ተጋድሎ ከየት ወዴት.pdf (1.0 MB)